15ኛው የእጅ መታጠብ ቀን በአለርት ኮምፕሬንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል “ንጹህ እጆች ለጤናችን ዋስትና ነው” በሚል መሪ ቃል ተከበሯል።
የዘንድሮው የእጅ መታጠብ ቀን በአለርት ሆስፒታል እንዲከበር የተወሰነው ሆስፒታሉ በጽዱ የጤና ተቋማት ኢኒሺዬቲቭ የተሻለ ተሞክሮ ስላለው መሆኑን የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ተናግረዋል።
የጤና ተቋማት በቂ የንጽህና መጠበቂያ እና የውሃ አቅርቦት ሊኖራቸው ይገባል ያሉት ዶ/ር ደረጀ፤ የእጅ መታጠብ ቀን ሲከበር “ጤናችን በእጃችን” ከሚለው መሪ ቃል በተያያዘ የዘንድሮው “ንጹህ እጆች ለጤናችን ዋስትና ነው” የሚለው መሪ ቃል መመረጡን ገልጸዋል።
በተለይም 6ኛው የዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የንጽህና አጠባበቅን እና የንጹህ ውሃ አቅርቦትን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ፤ በንጽና ጉድለት የሚከሰቱ በሽታዎችን በመከላከል የህጻናትን ከህልፈት መግታት ያስፈልጋል ብለዋል።